10 Feb, 2023
አዲሱ መንገድ በንፁህ ልብ እንድንጓዝበት ቂምን ጥሎ ይቅርታን አንጠልጥሎ ካልሆን የዘመን መቀያይር ምንም ጥቅም እንደሌለው በመድረኩ ላይ ታዳሚውን ዘና ኮስተር እያደረገ መራራ እውነቶችን አቀብሎናል። ስለዘጠኸን ጊዜ፣ክብር፣ትምህርት ከልብ እናመሰግናለን። በአዲሱ መንገድ ወደ ጣፋጭ ህይወት እንድንደርስ ልባችንን በፍፁም ይቅርታ እናፅዳው ።
ሁሌም ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ ይሄንን ጠዋት ያሳየኸኝ አምላክ ተመስገን ብዬ ነው የምጀምረው። ባለችኝ ነገር ደስተኛ ለመሆን እጥራለሁ። ጣፋጭ ህይወት ማለት የተሰጠንን ነገር እያመሰግንን በምስጋና መኖር ነው። ዛሬ ብሞት መንግስተ ሰማያት የምገባ የምግባ ይመስለኛል ምክንያቱም ልቤ ንፁህ ነው።በፍቅር ከሁሉ ጋር እኖራለሁ በጣፋጭ አንደበቷ ታዳሚውን ዘና እያረገች ከህይወቷ የተቀዱ ሀቆችን አጋርታናለች።ብሩህ ዘመን እንዲመጣ ልባችን ንፁህ ይሁን መልዕክቷም ነበር።
አጥሮቻችንን እስካልደረመስን ድረስ ዛሬም እንደትናንቱ ያመልጠናል ትናንት ላይ በብዙ ትዝታ ተመስጠን እያመለጠን ነው ዛሬ።ዛሬን በመኖር ነገን ብሩህ እናድርግ።