መጋቢት 22, 2015 ዓ.ም
የእኔ ነኝ መፍተሔው የአዎታዊነት እንቅስቃሴ በሀዋሳ ከተማ ሌዊ ሆቴል አንጋፋና ወጣት የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን ያቀርቡበት የኪነጥበብ ምሽት አካሄዷል። በምሽቱም አንጋፋዎቹ ገጣሚያን በለው ገበየሁና ዘመዱ ደምስስ ግጥሞቻቸውን ሲያቀርቡ ብሩክ ዚቲና ህይወት ተረፈ የመፍትሔ ሀሳቦች ላይ ንግግር አድርገዋል በሌላ በኩል የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ መቅርዝ የኪነጥበብ ቡድን ደግሞ ህብረ ዝማሬ ለታዳሚያን አቅርበዋል። እኔ ነኝ መፍትሔው የአዎታዊነት እንቅሰቃሴ ችግር ፈቺ ትውልድን ዜጋን ማብዛት፣ አሳባቢ ሳይሆን ትኩረቱን እራሱ ላይ ያደረገ በሙያው ድርሻውን በአግባቡ የሚወጣ ዜጋን መፍጠር ዓላማው ነው።
የእኔ ነኝ መፍትሔው ቀን2 በሐዋሳ የአዎታዊነት እንቅስቃሴ ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 23 2015 ዓ.ም ከሁለት መቶ ሀምሳ በላይ ተሳታፊዎች ቆሸሹ ሀሳቦችን እየጣሉ በጎ አድራጎትን ከውነዋል።
የእኔ ነኝ መፍትሔው የአዎታዊነት እንቅስቃሴ ዛሬ መጋቢት 22 2015 ዓ.ም በሐዋሳ ኤስ ኦ ኤስ ሄርማን ግማይነር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከነገ መፍትሔዎቻችን ጋር የነበርን ቆይታ!
መላውን የት/ቤቱን ማኔጅመንት እናመሰግናለን!
ቅዳሜ መጋቢት 23, 2015 ዓ.ም