06 Appril, 2024.
ቴድኔት ሚዲያና ኤቨንት ከራህዋ ኢንተርቴይመንት ጋር በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ::
ቴድኔት ሚዲያና ኤቨንት በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የተለያዮ የንግድ ኤክስፖዎችን የሙዚቃ ኮንሰርቶችን የንግድ ማስታወቂያዎችን የሚሰራ ድርጅት ነው።
ይህ ድርጅት በዛሬው ዕለትም በተለይ ለሀገራችን ድምፃዊያን የሚጠቅም ስምምነት መቀመጫውን ሲዊድን ካደረገውና ለረጅም አመታት የሀገራችንን ሙዚቀኞችን ወደ አውሮፖ በመውሠድና ከአውሮፖም ወደ ኢትዮጵያ ዘፋኞች እና ዲጄዎችን በማስመጣት ከሚታወቀው ራህዋ ኢንተርቴይመንት ጋር በጋራ የመስራት ስምምነት ፈፅመዋል::
ይህ ስምምነት በተለይ የሀገራችን ድምፃዊያን ወደ አውሮፖ በመሄድ ስራቸውን እንዲያቀርቡ ትልቅ መንገድ የሚከፍት ስምምነት ነው። በስምምነታቸው መሠረት ቴድኔት ሚዲያና ኤቨንት የራህዋ ኢንተርቴይመንት የኢትዮጵያ ወኪል ሆኖ ይሰራል። ቴድኔት ሚድያና ኤቨንት በአዲስ የፖድካስት እንዲሁም የውድድር ፕሮግራም በቅርቡ እየመጣ መሆኑንም የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ሲሳይ አሳውቀዋል።