ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም
ለአመታት አብሮን እየሰራ ያለው አጋራችን አዲስ ዕይታ በተባባሪ አዘጋጅነት የተሳተፈበት በሃገር ውስጥ እና የውጪ ገበያ የተሳሰሩ በግብርና፣ በሪል-ኢስቴት፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ ውጤቶች፣ ታዳሽ ሃይልና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እና ቱሪዝም ዘርፎችን በአንድነት ያጣመረ ኢትዮ- ኢንተርናሽናል ኤክስፖ ዛሬ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም ካሳንቺስ አካባቢ በሚገኘው በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በይፋ ተከፈተ። ኤክስፖ የሃገራችንን ኢኮኖሚ በኤክስፖርት ኢምፖርት እና የተለያዩ የሃገር ውስጥና ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትስስሮች አማካኝነት ለማሳደግ ያለመ ነው እንደሆነ ተገልጿል።
የንግድ አውደ ርዕዩ ከግብይት ባሻገር ነጻ ስልጠና፣ የስራ ትስስር፣ ነጻ የትምህርት ዕድል የተመቻቸለት ሲሆን በጊዜና በቦታ ርቀት መምጣት ለማይችሉ ካሉበት ቦታ ሁነው በኦንላይን መታደምም ሆነ መገበያየትም የሚያስችል መሆኑን በአውደ ርዕዩ ማስጀመሪያ ላይ አዘጋጆቹ ገልጸዋል። ዛሬ ግንቦት 9 ቀን የጀመረው የንግድ አውደ ርዕይ ለተከታዩቹ ሶስት ቀናት እስከ ግንቦት 11 ድረስ የሚቀጥል ሲሆን ዝግጅቱን በዋናነት ዓለም አቀፍ የገበያ አስተባባሪ የሆነው ትሬድ ኢትዮጵያ በዋናነት ሲያዘጋጀው አቡቀለምሲስ የሪል እስቴት ኢንስቲትዩት እና አዲስ ዕይታ በአጋርነት አዘጋጅተዋል።
ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም
ኣዲስ ኣበባ