መጋቢት 29, 2015
እኔ ነኝ መፍትሔው" የአዎታዊነት እንቅስቃሴ ዛሬ መጋቢት 29 አዳማ ከተማ በሚገኙ አምስት ትምህርት ቤቶች እናንተ ናችሁ መፍትሔዎቻችን በሚል የግንዛቤ የማስጨበጫ መርሐግብር አካሄድ።
ችግር ፈቺ ትውልድን ዜጋን ማብዛት፣ አሳባቢ ሳይሆን ትኩረቱን እራሱ ላይ ያደረገ በሙያው ድርሻውን በአግባቡ የሚወጣ ዜጋን መፍጠር ዓላማው የሆነው እኔ ነኝ መፍትሔው አዎንታዊነት እንቅስቃሴ በሀዋሳ ኤክስ ኤል ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ኬኛ ት/ቤት፣ ጎሮ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፣አዋሽ አካዳሚ ውስጥ ለሚገኙ ከ7000 ሺህ በላይ ተማሪዎች ስለ "እኔ ነኝ መፍትሔው" ፅንሰሀሳብ ግንዛቤ የማስጨበጥ መርሃግብሩን አካሄዷል።
በየት/ቤቶቹ ከሚገኙ ተማሪዎች እና መምህራን ጋር ስለመፍትሔው ሀሳቦች ውይይት ተካሄዷል። እኔ ነኝ መፍትሔው አዳማ በሚኖረው ቆይታ በቀጣይ ቀናት የተለያዩ ዝግጅቶችን ያከናውናል። ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 30 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ከአዳማ አለም ሆቴል ካፌ ፊትለፊት መነሻውን ያደረገ የእግር ጉዞ ወደ አዳማ ሳይንስ ዩንቨርሲቲ ያደረጋል። ለመሳተፍ መልካም ሀሳብ እና ቅን ልብ በቂ ነው ተብሏል ።
መጋቢት 29, 2016