ግንቦት 30
ሁለተኛው "ጣፋጭ ሕይወት ሽልማት" በትናንትናው እለት በካፒታል ሆቴል በድምቀት ተካሄዷል ለሁለተኛ ጊዜ "ጣፋጭ ሕይወት ሽልማት"የተሰኘ በማህበረሰባችን ላይ መልካም አሻራ እያሳረፉ የሚገኙ ሰዎችን እውቅና ክብር ምስጋና የምንሰጥበት ሌሎች ጀግኖቻችን የሚፈጠርበት መርሀ ግብር ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ስራ ፈጣሪዎች እንዲሁ ታዋቂ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በካፒታል ሆቴል ተካሂዷል። በስድስት ዘርፍ ሸልሟል።
፩. በስራ_ፈጠራ
፪. በአነቃቂ ንግግር
፫. በበጎ አድራጎት
፬. ዝናን ለመልካም ምግባር
፭. ሚድያውን_ለስነልቦና_ግንባታ
፮. ማህበራዊ ሚድያውን ለመልካምነት የተጠቀሙትን እያመሰገንን ሌሎች ጀግኖቻችን እናብዛ ።
ለሀገራችን የተስፋ የብርሀን ጮራን ይበልጥ ለማብራት በቅን ልባዊ ድርጊት ተሞልተን መልካም እየከወንን መልካም ሰሪዎች እያመሰገንን ጣፋጭ ህይወት እንስራም የሚል መልዕክት ተላልፏል።
ግንቦት 30