ባህርዳር
የአዎታዊነት እንቅስቃሴ ዛሬ ታህሳስ 14 ባህርዳር ከተማ በሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች እናንተ ናችሁ መፍትሔዎቻችን በሚል የግንዛቤ የማስጨበጫ መርሐግብር አካሄድ። ችግር ፈቺ ትውልድን ዜጋን ማብዛት፣ አሳባቢ ሳይሆን ትኩረቱን እራሱ ላይ ያደረገ በሙያው ድርሻውን በአግባቡ የሚወጣ ዜጋን መፍጠር ዓላማው የሆነው እኔ ነኝ መፍትሔው አዎንታዊነት እንቅስቃሴ በግዮን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ፣ ድልችቦ 1ኛ ደረጃ ፣ ሹምአቦ 2ኛ ደረጃ ፣አፄ ሰርፅድንግል አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ ከሚገኙ ከ4ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ስለ "እኔ ነኝ መፍትሔው" ፅንሰሀሳብ ግንዛቤ የማስጨበጥ መርሃግብሩን አካሄዷል። በየት/ቤቶቹ ከሚገኙ ተማሪዎች እና መምህራን ጋር ስለመፍትሔው ሀሳቦች ውይይት ተካሄዷል። እኔ ነኝ መፍትሔው በባህርዳር በሚኖረው ቆይታ በቀጣይ ቀናት የተለያዩ ዝግጅቶችን ያከናውናል። ነገ ቅዳሜ ታህሳስ 15 በባህርዳር ከተማ የወደቁ ኘላስቲኮችን እያነሳን ቆሻሻ ሀሳቦችን እንጥላለን የሚል የእግር ጉዞ እና የኪነጥበብ መሰናዶ በአንድ ላይ ያከናውናል። የዚህ ዝግጅት መነሻ ቦታ ፖሊ ዩኒቨርሲቲ ዋናው በር ፊት ለፊት መዳረሻ ቦታ ጣና ሆቴል ሲሆን ከጠዋት 2:00 አንስቶ መርሃግብሩ ይከናወናል ተብሏል። የቅዳሜው ዝግጅት የፅዳት ፕሮግራም፣ የእኔ ነኝ መፍትሔው ፅንሰ ሀሳብ ማስተዋወቅ፣ መዝናኛና ትውውቅን ያካትታል። ቅዳሜ ከሰዓት ደግሞ የበጎ አድራጎት ፍቅርን የማካፈል ምሳ ግብዣ ከድንበር የለሽ በጎ አድራጎት ጋር ይደረጋል። ለመሳተፍ መልካም ሀሳብ እና ቅን ልብ በቂ ነው ተብሏል ።
ቀን 1
ዛሬ በባህርዳር ከተማ "የወደቁ ኘላስቲኮችን እያነሳን ቆሻሻ ሀሳቦችን እንጥላለን " የተሰኘ የእኔ ነኝ መፍትሔው አዎንታዊ እንቅስቃሴ ቀጣይ መርሃግብር ተካሄደ። ከተለያዩ የባህርዳር ከተማ ማህበረሰብ አባላት ጋር በመሆን በጣና ዳር የእግረኛ መንገድ የእግር ጉዞ የተካሄደ ሲሆን የመፍትሔ ሀሳቦች ላይም ውይይት ተከናውኗል። የዛሬው መሰናዶው ከውይይትም ባሻገር የእኔ ነኝ መፍትሔው ፅንሰ ሀሳብን ማስተዋወቅ፣ መዝናኛና ትውውቅን ያካተተም ነበር። በእለቱም የፕላስቲክ ቆሻሻ ከጣና ሀይቅ አካባቢ በመሰብሰብ እንዲወገድ ተደርጓል። ከ5:00 በኃላም በጣና ሆቴል ግቢ ውስጥም የተለያዩ የሰርከስ ፣ የግጥም ፣ ስለእኔ ነኝ መፍትሔው ሀሳቦች ላይ ትኩረቱን ያደርገ የኪነጥበብ መሰናዶ ተካሄዷል። የአዎንታዊነት እንቅስቃሴውን እንዲሳካ በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ ላደርጉ ተቋማትና ግለሰቦች የእውቅና አሰጣጥ መርሐግብር ላይ ተከናውኗል። እኔ ነኝ መፍትሔው የአዎታዊነት እንቅሰቃሴ ችግር ፈቺ ትውልድን ዜጋን ማብዛት፣ አሳባቢ ሳይሆን ትኩረቱን እራሱ ላይ ያደረገ በሙያው ድርሻውን በአግባቡ የሚወጣ ዜጋን መፍጠር ዓላማው ነው።
ቀን 2
ዛሬ እኔ ነኝ መፍትሔው የአዎታዊነት እንቅስቃሴ በባህርዳር ቆይታው በዝግባ የህጻናትና አረጋዊያን መርጃ ለአረጋውያኑ ጋር ፍቅር የማካፈልን ምሳ ነጋበዝ ለአረጋውያኑ።መሰረት በጎ አድራጎት ድርጅትን የባህዳሩን ቅርንጫፍ ጉብኝት ከድንበር የለሽ የበጎ አድራጎት ማህበር ጋር አካሄዷል። የእኔ ነኝ መፍትሔው አባላት በድርጅቱ ውስጥ ከሚገኙ አረጋዊያን ጋር ምሳ አብረው የተመገቡ ሲሆን ከአባቶችም ትልቅ በረከት የሆነውን ምርቃት ተቀብለዋል።አባቶችን እናንተም ናችሁ መፍትሔውቻችን በፀሎታችሁ አስቡንም ተብለዋል። በተጨማሪም ከዝግባ የህጻናትና አረጋዊያን መርጃ በጎ አድራጎት ድርጅት ኃላፊዎችም ጋር በቀጣይ ስለሚሰሩ ስራዎች ላይም ውይይት ተካሄዷል። እኔ ነኝ መፍትሔው የአዎታዊነት እንቅሰቃሴ ችግር ፈቺ ትውልድን ዜጋን ማብዛት፣ አሳባቢ ሳይሆን ትኩረቱን እራሱ ላይ ያደረገ በሙያው ድርሻውን በአግባቡ የሚወጣ ዜጋን መፍጠር ዓላማው ነው።
ቀን 3 በጎ አድራጎት
እኔ ነኝ መፍትሔው የባህርዳር ቆይታው! ተስፋ፣ፍቅር፣ብርታትን የሰነቅንባቸው ሶስት አስደናቂ ቀናት በውቢቷ ባህርዳር። እኔ ነኝ መፍትሔው የአዎታዊነት እንቅስቃሴ በባህርዳር ከተማ ከታህሳስ 14 እስከ 16 የተለያዩ ውጤታማ ስራዎችን አከናውኗል። "እኔ ነኝ መፍትሔው" የአዎታዊነት እንቅስቃሴ በመጀመሪያው ቀን (ታህሳስ 14) ባህርዳር ከተማ በሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች በግዮን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ፣ ድልችቦ 1ኛ ደረጃ ፣ ሹምአቦ 2ኛ ደረጃ ፣አፄ ሰርፅድንግል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች ከ4ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ስለ "እኔ ነኝ መፍትሔው" ፅንሰሀሳብ ግንዛቤ የማስጨበጥ መርሃግብሩን አካሄዷል። በየት/ቤቶቹ ከሚገኙ ተማሪዎች እና መምህራን ጋር ስለመፍትሔ ሀሳቦች ውይይት ተደርጎበትም ነበር። በቀጣይ ቀን ታህሳስ 15(ቅዳሜ) "የወደቁ ኘላስቲኮችን እያነሳን ቆሻሻ ሀሳቦችን እንጥላለን " የተሰኘ የእኔ ነኝ መፍትሔው አዎንታዊ እንቅስቃሴ ቀጣይ መርሃግብር ተካሄዷል። ከተለያዩ የባህርዳር ከተማ ማህበረሰብ አባላት ጋር በመሆን በጣና ዳር የእግረኛ መንገድ የእግር ጉዞ የተካሄደ ሲሆን የመፍትሔ ሀሳቦች ላይም ውይይት ተከናውኗል። መሰናዶው ከውይይትም ባሻገር የእኔ ነኝ መፍትሔው ፅንሰ ሀሳብን ማስተዋወቅ፣ መዝናኛና ትውውቅን ያካተተም ነበር። በእለቱም የፕላስቲክ ቆሻሻ ከጣና ሀይቅ አካባቢ በመሰብሰብ እንዲወገድ ተደርጓል። በመጨረሻም በዝግባ የህጻናትና አረጋዊያን መርጃ በጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ ከድንበር የለሽ የበጎ አድራጎት ማህበር ጋር በመሆን ፍቅርን የማካፈል ምሳ የግብዣ አካሄዷል። እኔ ነኝ መፍትሔው የአዎታዊነት እንቅሰቃሴ በቀጣይ በሌሎች ከተሞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቱን ያከናውናል።
ባህርዳር